
ስለ እኛ
እጅግ የላቁ የሶላር ቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን በዓለም ዙሪያ በማቅረብ ላይ እንገኛለን።
ታሪካችን
SPWES LLC በቫንኮቨር፣ ዋሽንግተን፣ ዩኤስኤ ላይ የተመሰረተ እና በኢትዮጵያ፣ አፍሪካ ተደራሽነቱን ያስፋፋ ግንባር ቀደም የምህንድስና ድርጅት ነው። በሶላር ጀነሬተሮች፣ በኃይል ማከማቻ፣ በቢኤምኤስ፣ በሶላር ፓምፖች መፍትሄዎች እና በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያ ጣቢያዎች ላይ በመመርኮዝ ዘላቂነት ባለው ቁርጠኝነት ፈር-ቀዳጅ መፍትሄዎችን በማቅረብ የላቅን እንገኛለን። ተልእኳችን ዘላቂ የኃይል እና የውሃ ኢንጂነሪንግ መፍትሄዎችን ማቅረብ፣ ፕላኔታችንን ለትውልድ በመጠበቅ ግለሰቦችን፣ ማህበረሰቦችን እንዲሁም የንግድ ተቋማትን እንዲበለጽጉ ማበረታታት ነው።

ራዕያችን
በ SPWES LLC ፥ ራዕያችን የዓለምአቀፍ የኃይል አቅርቦት እና የውሃ ተደራሽነት ገጽታን በአብዮታዊ መንገድ መምራት ነው። ለሁሉም ተደራሽ እና ለአካባቢ ተስማሚ የኃይል እና የውሃ ምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረብ የዘላቂ እድገት ምልክት ለመሆን ጠንክረን እንሰራለን። ዋና ግባችን የታዳሽ ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን ኃይል በመጠቀም ንፁህና ዘላቂነት ላለው ዓለም አስተዋፅዖ ማድረግ ነው።
ቡድናችን የተለያዩ ክህሎቶች እና ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎችን ያካትታል፤ እንዲሁም የሚከተሉትን ጨምሮ ፡-
-
ከፍተኛ የቮልቴጅ ኃይል ስርዓቶች፡- ለተቀላጠፈ የኃይል ስርጭት እና አጠቃቀም ከፍተኛ አፈጻጸም ያላቸውን ከፍተኛ-ቮልቴጅ የኃይል ስርዓቶችን እንነድፋለን።
-
የኃይል ኤሌክትሮኒክስ፡- በኃይል ኤሌክትሮኒክስ ፥ ግንባር ቀደም የኃይል ልወጣን እና አስተዳደርን ለማመቻቸት የላቁ ሥርዓቶችን እናዘጋጃለን።
-
ኢንቮርተር ልማት፡- የሶላር ጀነሬተሮችን እና የኃይል ማከማቻ ስርዓቶችን አፈፃፀም የሚያሻሽሉ ዘመናዊ ኢንቬንተሮችን በመንደፍ እና በማምረት ላይ እንሰራለን።
-
የባትሪ አስተዳደር ሲስተምስ (BMS)፡- የላቀ የቢኤምኤስ መፍትሔዎቻችን የሊቲየም ባትሪ ሞጁሎችን ደህንነትን፣ ረጅም ዕድሜን እና ቅልጥፍናን ያረጋግጣሉ።
-
የሊቲየም ባትሪ ሞጁል እና የባትሪ መደርደሪያ ልማት፡- የሊቲየም ባትሪ ሞጁሎችን እና መደርደሪያዎችን ወደ ልዩ የፕሮጀክት መስፈርቶች እንዲሁም እንደ ደንበኞቻችን ፍላጎት እናዘጋጃለን።

ክህሎቶቻችን

ዓለም አቀፍ ተደራሽነት
ዋና መሥሪያ ቤታችን በቫንኮቨር ዋሽንግተን ቢሆንም እውቀታችንን እና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ለአፍሪካ አህጉር አስፋፍተናል ፤ በተለይም በኢትዮጵያ ጉልህ ስፍራ አለን። በእነዚህ የተለያዩ ክልሎች ውስጥ ዘላቂ የኃይል መፍትሄዎችን በማቅረባችን እና በማሳደጋችን እንዲሁም ማህበረሰቦች እንዲበለጽጉ እና ንግዶች እንዲስፋፉ በማገዛችን ኩራት ይሰማናል።
በSPWES LLC፣ ዘላቂነት እያንዳንዱ ጥረታችንን ይመራል። የካርቦን መጠን ዱካችንን በመቀነስ እና ኃላፊነት የሚሰማውን የአካባቢ ጥበቃን ለመደገፍ ቅድሚያ እንሰጣለን። የእኛ መፍትሄዎች የኃይል ወጪዎችን እንዲሁም የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀትን በመቀነስ አረንጓዴ የሆነ ነገን እና ዘላቂነት ያለው አስተዋጽኦን ያደርጋል።

ቁርጠኝነታችን

ለአካባቢ ተስማሚ
እንደ ፍላጎቶ የተዘጋጀ ንድፍ
ለግብርና ዓላማ በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ ፓምፖችን እናቀርባለን።
በብዙ አገሮች ውስጥ ያገኙናል።
12+ ሰዓቶች በላይ የሚቆይ ተጠባባቂ ባትሪ
ይወቁን!
ዘላቂ የኃይል እና የውሃ ኢንጂነሪንግ መፍትሄዎችን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ በተልዕኳችን እንድትሳተፉ እንጋብዝዎታለን። ከSPWES LLC ጋር ለመተባበር ፍላጎት ካልዎት ወይም ስለእኛ አዳዲስ ምርቶች እና አገልግሎቶቻችን የበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ ፤ እባክዎ መልእክት ያስቀምጡልን።